ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረቡትን የመያዣ ንብረቶች በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ወጋገን ባንክ አ.ማ
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር፡ ወጋገን 041/2018
ወጋገን ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት ከዚህ በታች የቀረቡትን የመያዣ ንብረቶች በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የተሽከርካሪው
ዓይነት |
የሰሌዳ ቁጥር | የሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | ዘመን | የነዳጅ
አይነት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር | ጨረታው የሚከናወንበት ጊዜ | |
| ቀን | ሰዓት | |||||||||||
| 1 | ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/
ማህበር |
ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/
ማህበር |
ጎፋ |
አስፋልት ዲስትሪቢዩተር (ልዩ ተንቀሳቃሽ) | ET-03-A13868 | YV2VBL0C3JZ115884 | D7E280EC112087527 | 2017 | ናፍጣ | 7,000,000.00 | መስከረም
07 ቀን 2019 |
ከጧቱ 3፡00 –
6፡00 ሰዓት |
| የጭነት ሲኖትራክ | ET-03-A15922 | LZZ5BLNF6MN896201 | WD615.69*210707026177* | 2021 | ናፍጣ | 2,500,000.00 | ||||||
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ (አንድ አራተኛ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት በጨረታው ዕለት በመቅረብና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ቀሪውን ገንዘብ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣ ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ለሆነ፤ የባንኩን የብድር ፖሊሲ፤ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟላ፣ እንዲሁም ተጨማሪ የመያዣ ንብረት ለሚያቀርብ ተጫራች ባንኩ በውስጥ የብድር መመሪያ መሰረት ብድር ሊያመቻች ይችላል፡፡
- የተጫራቾች የምዝገባ ሰዓት፤ ከጧቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሲሆን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለእያንዳንዱ ንብረት የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ነው፡፡ ሆኖም የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው ይቀጥላል፡፡
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ካካሄደው ከባንኩ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡
- ጨረታው በባንኩ ዋና መስርያ ቤት ህንጻ 9ኛ ፎቅ ላይ ባለው የመሰብሰብያ አዳራሽ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
- ለሀራጅ ጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፊት ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡
- ተበዳሪው /ንብረት አስያዥ/ ወይም ሁለቱም በጨረታው ቀን እና ሰዓት በቦታው ላይ መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ተበዳሪው /ንብረት አስያዡ/ በጨረታ ቀን እና ሰዓት በቦታው ባይገኝ ጨረታው በሌለበት ይካሄዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም የተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡
- ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ የጨረታው አሸናፊ የሚከፍል ይሆናል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት ወጋገን ባንክ አ.ማ የብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት 011-558-18-37፣ መደወል ይችላሉ፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ወጋገን ባንክ አ.ማ
