የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ብራና ማተሚያ ድርጅት ተገቢ ዕድሳት የተደረገላቸው (Refurbished) ና በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ ማሽኖች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 010/2017
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ብራና ማተሚያ ድርጅት ተገቢ ዕድሳት የተደረገላቸው (Refurbished) ና በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ ማሽኖች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መሳተፍ ትችላላችሁ።
1ኛ በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ፣
2ኛ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3ኛ የግብር ከፋይነት መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
4ኛ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
5ኛ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
6ኛ በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በአቅራቢነት ለመመዝገባቸው ማስረጃ ያላቸው፤
7ኛ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር አምስት መቶ (500.00) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ) ወሎ ሰፈር በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 32 በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
8ኛ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ያቀረቡትን ዋጋ 2% በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
9ኛ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማስረከቢያ ጊዜ መጥቀስ አለባቸው፣
10ኛ ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፏቸውን ማሽኖች ድርጅቱ መጋዘን ድረስ ማድረስ አለባቸው፣
11ኛ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 11ኛው የሥራ ቀን እስከ 8፡00 (ከሰዓት) ድረስ በሰም በታሸገ ፖስታ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
12ኛ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ በሚወስደው መንገድ 700 ሜትር ላይ በስተግራ በኩል
ስልክ ቁጥር፡- 0114 42 64 80
ብራና ማተሚያ ድርጅት
