ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒየን የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ዩንየን በዩንየኖችና ሕብረት ስራ ማህበራት መጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ
የጨረታ ማስታወቂያ
ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒየን የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ዩንየን በዩንየኖችና ሕብረት ስራ ማህበራት መጋዘን ተከማችቶ የሚገኘውን ለምርት ግብዓት የማይውል የተለያዩ የአፈር ማዳበሪያ በጨረታ አወዳድሮ እንዲሸጥ በተወሰነው መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላችሁ ግለሰብ ወይም ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ግዴታዎች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶችም፤
- ለምርት ግብዕት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ (Expired) የስራ ፈቃድ ያለው፣ የ2017 ዓ.ም የታደሰ ሥራ ፊቃድ፣ TIN ግብር ስለመክፈሉ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ይህንን ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደር እንደማያቀርቡ እና አቅርበው የሚገኙ ከሆነ በህግ ስለመጠየቃቸው የሚያስረዳ ደብዳቤ ለሮቢ በርጋ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንየን ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ጠቅላላ የተወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 8% CPO በኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በሮቢ በርጋ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩንየን ስም ማቅረብ ያለባችሁ ሲሆን፤ የጨረታው ማስከበሪያ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ሲመለስ፤ ለአሸናፊዎች ግን ሥራውን በተዋዋሉት መሠረት ሲያጠናቅቁ አፈፃፀማቸው ታይቶ እና ተረጋግጦ የሚመለስላቸው ይሆናል።
- ተጫራቾች በዩንየኑ መጋዘን በአካል በመገኘት ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ ያለበትን ሁኔታ በማየት የተዘጋጀውን ሰነድ በብር 2,000 በመግዛት፤ ለእያንዳንዱ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ የሚገዙበትን የአንድ ኩንታል ዋጋ ዩንየኑ በሚሰጠው የመነሻ ዋጋ በብር መስጠት አለባቸው።
- ተጫራቾች/ተወካዮቻቸው/ በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅቱ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡05 ሰዓት በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- ተጫራቾች የማስጫኛ ዋጋ በራሳቸው የሚችሉ ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በአምስት ቀን ውስጥ ለምርት ግብዓት የማይውል የአፈር ማዳበሪያ በዩንየኑ መጋዘን ውስጥ ተሰብስቦ የሚገኘውን በመለየት በወቅቱ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የሚረከቡ ይሆናል።
- ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎችን ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ በመለየት በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ማሕተም፣ ስም እና ፊርማ ተደርጎበት መቅረብ አለበት።
- ዩኒየኑ በጨረታው ላይ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፤- ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒየን ሆለታ ከተማ ግብርና ምርምር በሚወስደው መንገድ
ስልክ ቁጥር 0913-93-75-36/07-07-43-47-49
በምዕራብ ሸዋ ዞን አስተዳደር ሮቢ በርጋ የገ/ሕ/ሥራ ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ
