በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩከ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሲገለገልባቸው የቆዩ ጀነሬተሮችን በሀራጅ የጨረታ ሽያጭ እቃዎቹ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሀራጅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩከ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሲገለገልባቸው የቆዩ ጀነሬተሮችን በሀራጅ የጨረታ ሽያጭ እቃዎቹ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም፡-
- በሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ 2፡00-6፡00 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሀብት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በመምጣት መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች በሀራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የ 50,000 ብር CPO በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተ.ቁ |
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም |
የጨረታው ዓይነት |
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ |
የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት |
የሐራጅ ጨረታ |
እስከ 02/10/2017 ዓ.ም |
02/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ይከፈታል |
- የጨረታው መክፈቻ ቦታ: በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናል ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ያስያዙትን ዋስትና CPO በተመለከተ ለአሸናፊው ካሸነፉት የእቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤት በተገለጸ በሶስት (03) የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህንን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው በሌላ የማስወገጃ መንገድ የሚወገድ ሲሆን ነገር ግን የእቃውን ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል። ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሌላ አማራጭ ይወገዳል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይንም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- በመመሪያ ቁጥር 9/2003 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ 3 ለ መሰረት በሀራጅ ጨረታው ወቅት ከሀራጁ መሪ አማካኝነት የጨረታው መነሻ ዋጋ የሚቀመጥ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
