በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስ/ር ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እሰከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለ6 ወራት በህግ ጥላ ስር በመታረም ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብና አገልግሎት የሚውል፡- እህል ፤ ማጣፈጫ ቅመማ ቅመም፣ ንፁህ የምግብ ዘይት፤ ስኳር እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስ/ር ኮሚሽን በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ እሰከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለ6 ወራት በህግ ጥላ ስር በመታረም ላይ ለሚገኙ ለህግ ታራሚዎች ምግብና አገልግሎት የሚውል፡- እህል ፤ ማጣፈጫ ቅመማ ቅመም፣ ንፁህ የምግብ ዘይት፤ ስኳር እና የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ ንግድ ፍቃድ ያለው።
- የዘመኑን ግብር የከፈለ ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።
- የግብር መለያ /Tin ቁጥር ያለው።
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ፣ CPO በጥሬ ገንዘብ የተረጋገጠ 15,000.00 /አሥራ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከ 1 እስከ 5 የተጠቀሰውን ማስረጃዎችን እና የመጫረቻ ሠነድ አርጅናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማስገባት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግስት የሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ ጨረታ ሠነድ የማይመለስ 300 /ሦስት መቶ ብር /በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ዕቃውን በራሳቸው ወጪ እስከ ሣውላ ማረሚያ ተቋም አምጥተው ማስረከብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊዎች ሆነው የተገኙ ተጫራቾች የዕቃዎችን አጠቃላይ ዋጋ በ10% ቼክ ወይም /CPO/ የውል ማስከበርያ በማስያዝ ከሣውላ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት ጋር የውል ስምምነት መፈፀም ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ከሁሉም ዓይነት ናሙና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫረቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ዕለቱ ቅዳሜ እሁድ እና በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በመንግስት ሥራ ሰዓት ይከፈታል።
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መወዳደር ተቀባይነት የለውም።
- ማረሚያ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሣውላ ማረሚያ ተቋም የግዥ ፋ/ን/አስ/ር ደጋፊ ሥራ ሂደት
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0467770041/0916479909
በጎፋ ዞን የሣውላ ማረሚያ ተቋም
