Tender Detail

Tender Details

  • Company የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ጽ/ቤት
  • Address ባሌ ዞን ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 02224400023
  • Website
  • Deadline13 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-06-13 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Firewood

የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት በማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውሉ ከሀምሌ 01 ቀን 2017 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ የሚቀርብ የምግብ እህሎች ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች እና ድፍን የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር // 05/2017

 

የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት በማረሚያ ቤቱ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውሉ ከሀምሌ 01 ቀን 2017 / እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 / ድረስ የሚቀርብ የምግብ እህሎች ማጣፈጫ ቅመማ ቅመሞች እና ድፍን የማገዶ እንጨት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የንግድ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ 2017 . የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን (Trade license) የንግድ ምዝገባ ወረቀት: የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የቲኦቲ (TOT) የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርተፍኬት ምዝገባ ማስረጃ: የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (Supplier list) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ከባሌ ዞን ማረሚያ ቤት ከቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር) የያዘ ሲፒኦ ብቻ ህጋዊ እውቅና ካለው ባንክ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና የቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ 2017 . የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን (Trade license) የንግድ ምዝገባ ወረቀት: የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ሰርተፍኬት የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (Supplier list) ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች በመግዛት ኦሪጂናል ፋይናንሺያል (ዋጋ የተሞላበት) ሰነድ ፋይናንሺያል ኮፒ ሰነድ እንዲሁም ቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ ሶስቱንም ሰነዶች በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት እለት እና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  6. እያንዳንዱ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት።
  7. ጨረታው በጋዜጣ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
  8. በጥቃቅን እና አነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
  9. ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው 5 ቀን በኋላ 6ኛው ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ውስጥ /ቤቱ ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው። ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር፡- 022 244 00023/09 32 31 12 24 ደውለው ይጠይቁ።

 

የባሌ ዞን ማረሚያ ቤት

 

Save Tender