Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የአርባምንጭ ማረሚያ ተቋም
  • Address አርባምንጭ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 881 0049
  • Website
  • Deadline14 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-06-14 00:00:00
  • Categories Animals , Animal Feed And Supply , Firewood

የአርባ ምንጭ ማረሚያ ተቋም በህግ ጥላ ሥር ለሚገኙ ህግ ታራሚዎች ለ2018 በጀት ዓመት የሚሆን የተለያየ ዓይነት የመኖ እህልና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማሳወጅ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአርባ ምንጭ ማረሚያ ተቋም በህግ ጥላ ሥር ለሚገኙ ህግ ታራሚዎች 2018 በጀት ዓመት የሚሆን የተለያየ ዓይነት የመኖ እህልና የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማሳወጅ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት፡-

  1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  3. የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሌሎች ይጠቅመኛል ካሉት መረጃ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል ሆኖ ከላይ በተገለጸው ዝርዝር መሰረት ተጫራቾች
  • የጨረታውን ዝርዝር የሚገልጽ ሰነድ አርባምንጭ ማረሚያ ተቋም ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ 200.00 ሁለት መቶ ብር ብቻ ከፍሎ ሰነዱን በመውሰድ፤
  • የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 አሥር ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ አርባምንጭ ማረሚያ ተቋም ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ፖስታ ውስጥ በማስገባት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከጠዋቱ 230 እስከ 1130 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል።
  • ጨረታው የሚከፈተው 16ኛው ቀን 430 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 500 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፤ ዕሁድና የበዓላት ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል
  • በጨረታው አሸናፊ የሆነው ያሸነፈውን እህልና ማገዶ እንጨት ማሸነፉ ሲረጋገጥ ቀርቦ ውል በመግባት በራሱ ወጪ እስከማረሚያ ተቋም ጊቢ ድረስ በማምጣት ያስረክባል።

ማሳሰቢያ፡- የተጫራቾች መገኘት አለመገኘት የጨረታውን መክፈቻ ሂደት አያስተጓጉልዎ።

  • ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ፡-

ስልክ ቁጥር 046 881 0049 እና 046 881 0093 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የአርባምንጭ ማረሚያ ተቋም

 

Save Tender