Tender Detail

Tender Details

  • Company City Government of Addis Ababa Office of the auditor General (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት)
  • Address ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ከፊሊፕስ ህንፃ ከፍ ብሎ ከማይጨዉ ክሊኒክ ጀርባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ህንፃ ላይ 9ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115-58-07-15
  • Websitehttps://www.aaag.gov.et/
  • Deadline11 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-06-11 00:00:00
  • Categories Maintenance And Repair , Office Machines And Computers , Electronics Materials

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተለያየ የቢሮ መገልገያ ማሽኖች ማለትም ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተሮች፣ ከለር ፕሪንተሮች፣ ኤልሲዲ ፕሮጀክተሮች፣ ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች የመሳሳሉ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችን የጥገና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት የሚቆይ የጥገና አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

መለያ ቁጥር 002/2017.

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር /ቤት 2017 በጀት ዓመት የተለያየ የቢሮ መገልገያ ማሽኖች ማለትም ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተሮች፣ ከለር ፕሪንተሮች፣ ኤልሲዲ ፕሮጀክተሮች፣ ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች የመሳሳሉ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችን የጥገና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት የሚቆይ የጥገና አገልግሎት መግዛት ስለሚፈልግ በዘርፉ በቂ ልምድና ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

በጨረታውን የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው፡-

  • ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  • በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ፣
  • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚጫረቱበትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2,000.00/ሁለት ሺህ/ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት የስራ ከፍል መግዛት ይችላሉ።
  • ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን /ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም፣ ፊርማ በማሳረፍ እና ሙሉ አድርሻቸውን በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር /ቤት ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ጨረታው 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ 11ኛው ቀን 3:30 ሰዓት ከታሸገ በኋላ በዕለቱ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም 11ኛው ቀን የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ማንኛውም ተጫራች ዋጋውን በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115-58-07-15 ወይም 0911-36-05-27 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ከፊሊፕስ ህንፃ ከፍ ብሎ ከማይጨዉ ሊኒክ ጀርባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ህንፃ ላይ 9 ፎቅ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር /ቤት

 

Save Tender