በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል 1. የተለያየ ፈርኒቸሮች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 11/2017
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል 1. የተለያየ ፈርኒቸሮች ግዢ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው፣
- የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግዢው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 - 5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ዓይነት፣ የአምራቹን ስም፣ የተመረተበትን ዓ.ም በዝርዝር ከዋናው ጋር መያያዝ አለበት።
- ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ሲጠየቅ ማቅረብ አለበት፤
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም ቢድ ቦንድ ከሆነ 60 እና ከዚያ በላይ ቀናት የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በጉ/ዞ/ገ/ባ/ዋ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃውን ጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ወልቂጤ ከተማ ድረስ ለማቅረብ የሚያስችል ዋጋ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ ታሽጐ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት ጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱ ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 በይፋ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011330012 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊዎች ላቀረቡት እቃዎች የእጅ በእጅ ደረሰኝ ተጠቃሚ ከሆኑ ከገቢዎች የማረጋገጫ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን እንዳለበት እንገልፃለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የጉራጌ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ
