Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-2-20-59-92
  • Website
  • Deadline16 Jun 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date2025-06-16 00:00:00
  • Categories Agriculture And Farming , Food And Beverage

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በኬሚካል የታሸ እና ከዘርነት የወደቀ በቆሎ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 008/ሽያጭ/17 /

 

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በኬሚካል የታ እና ከዘርነት የወደቀ በቆሎ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም: -

  1. ተጫራቾች በሪሳይክል ሥራ ዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችኋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ /CPO/ በደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት ስም ከጨረታ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው በድርጅቱ የግዥ ፋይንናስ ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማንኛውም በማይለቅ ማሸጊያ በታሸገ ፖስታ /ኤንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ እስከ 800 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ሳጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 830 ሰዓት በድርጅቱ የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ፣ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን የተረፈ ምርት ዓይነቶችን የተከማቸበት መጋዘን በአካል በመቅረብ ናሙና በማየት በናሙናው መሠረት የአንድ ኪሎ ግራም ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ ስማቸውን፣ ፈርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  6. ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ የጨረታ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ቀርቦ ቢገኝ ተጫራቹ ጨረታውን ከመሳተፍ ይታገዳል፡፡
  7. ድርጅቱ ለዚህ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የደቡብ ምርጥ ዘር ደርጅት

 

Save Tender