በአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ ወይም ለምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል እና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን እንዲሁም የማገዶ እንጨት በ2018 በጀት ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለ6 ወር (ስድስት ወር) በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ ወይም ለምግብ አቅርቦት የሚውል ጥሬ እህል እና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን እንዲሁም የማገዶ እንጨት በ2018 በጀት ከሐምሌ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለ6 ወር (ስድስት ወር) በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት ማንኛውም ጨረታውን ለመካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡-
-
- ተወዳዳሪዎች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ ውስጥ የተመዘገቡና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና አግባብነት ያለው የ2017 የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) የተመዘገቡ ወይም የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የዞን ማራሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት ውስጥ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾቹ የጨረታ ማስከበሪያ ከመቶ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም የተመሰከረለት ቼክ እና የምግብ እህል ናሙና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል። ይህ ካልተገኘ በጥሬ እህል እናወዳድራለን፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት በዞን ማረሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎች እና የማረሚያ ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ይከፈታል።
- የዞኑ ማራሚያ ቤት አስተዳደር ፅ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀው ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስለው ማቅረብ የሚችሉ፤
- ማረሚያ ቤቱ የሚገኝበት ከተማ በአርሲ ዞን አሰላ ማረሚያ ቤት፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-331-1040/ 09 13-43 99 72
በኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የአርሲ ዞን ማረሚያ ቤት
