የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኝ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የዕጣን ምርት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ
የዕጣን ምርት ሽያጭ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ - ኢምዘደውአዘ/ግጨ/ሸ02/2017
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የሚገኝ የተለያዩ ዓይነትና ደረጃ ያላቸው የዕጣን ምርት ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከ7፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት) አዲስ አበባ በሚገኘው በዘርፍ ጽ/ቤት ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4 እና የማይመለስ ብር 200,00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ2% ያላነሰ በCPO በኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል የጨረታው ዋጋ ለ 60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል። የዕጣን ምርት ሽያጭ ተጫራቹ በሚሰጠው ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይጨምራል።
- ጨረታው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረበው የዕጣን ምርት መጫረት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ዘርፉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስልክ 011 6 18 61 25
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ
