በቤ/ጉ/ክ/መ/ የአሶሳ ዞን ማ/ቤቶች በ2018 የበጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ እህል የወጥ እህል እና የፅዳት እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ ማስታወቂያ
በቤ/ጉ/ክ/መ/ የአሶሳ ዞን ማ/ቤቶች በ2018 የበጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የተለያየ እህል የወጥ እህል እና የፅዳት እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ለተጫራቾች የተዘጋጀ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ነው::
የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ከሐምሌ 01 ቀን 2017 እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ያለውን ቀለብና የተለያዩ የወጥ እህሎች እና የንፅህና እቃዎችን ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከተውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሠርገኛ ጤፍ፣ ነጭ ማሽላ፣ ጥራት ያለው በቆሎ፣ ከአተር የተፈጨ ሽሮ፣ ሻይ ቅጠል፣ ኤግል ካሜራ (እርሾ)፣ ከኖር የወጥ ማጣፈጫ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ በርበሬ፣ ፓስታ፣ አጃክስ፣ ጨው፣ ባቄላ ክክ፣ ሩዝ የሚቀቀል፣ ድንች፣ የዳቦ ዱቄት፣ ኑግ፣ ስኳር፣ የምግብ ዘይት፣ ማጂ ማክስ (Magi Max) ዳቦ ማሻሻያ፣ ምስር ክክ፣ አተር ክክ እና የልብስ ሳሙና 250 ግራም በጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች -
- በተሰማሩበት የስራ መስከ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፦
- የገንዘብ ሚኒስቴር/ የክልሉ ገ/ኢ/ል/ቢሮ የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት / ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡-
- ተጫራቾች እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ እና የውል ስምምነት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት አሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቢሮ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ማስያዣ/10,000/ አስር ሺህ ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በተቋሙ በመገኘት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን በሙሉ ወይም በከፊል በመሙላት መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፤
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 7፡30 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ዕለት ባይገኙም የጨረታ አከፋፈት ሂደቱ አይስተጓጎልም ፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀናት በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው በሚከፈትበት አብሮ መቅረብ አለበት ፡፡
- ቫት ተመዝጋቢ ወይንም ቲኦቲ ደረሰኝ ያሳተሙ መሆን አለባቸው።
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09-17-85-62-51/09-12-79-31-46
ማሳሰቢያ፡- ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት በገዛችሁት ሰነድ ብቻ ይሆናል፡፡
ሰነዱ አስፈላጊው መረጃ ተሞልቶና የድርጅቱ ማሕተም ተመትቶ ከዋጋ ዝርዝር ጋር የሚመለስ ይሆናል።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክ/መ/የአሶሳ ዞን ማ/ቤቶች መምሪያ
