ኮርፖሬሽናችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን የአስፖልት አስፖልት ፕላንት ገጠማ፤ ተከላ እና የተሳካ ሙከራ ለማስደረግ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ኮርፖሬሽናችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን የአስፖልት አስፖልት ፕላንት ገጠማ፤ ተከላ እና የተሳካ ሙከራ ለማስደረግ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የማሽኑ አይነት |
የማሽኑ ሞዴል |
መለኪያ |
ብዛት |
የሚተከልበት ቦታ |
ምርመራ |
|
1 |
የአስፖልት ፕላንት |
Speco Asphalt plant (TSAP-1500) |
በቁጥር |
01 |
ወልዲያ ከተማ |
|
ስለዚህ ከዚህ በታች የተለገፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የንግድ ፈቃድ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት የምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (VAT) ያላቸው መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲ.ፒ.ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል የባንክ ጋራንቲ የተ.እ.ታክስን ጨምሮ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በኮርፖሬሽናችን ስም ማለትም “ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (Hibir Construction Corporation”) ለ 90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያው የፋይናንሻል ፖስታ ዋና (ኦርጅናል) ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን ፋይናንሻል ፖስታ ኮፒ (ቅጅ) እና ኦርጅናል (ዋና) በማለት በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከኮርፖሬሽናችን ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ዋጋ እና የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሀያ ቀናት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ዋና መ/ቤታችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት ግዥ ቢሮ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ20ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 መደወል ይችላሉ።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ባህር ዳር
