መ/ቤታችን የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን በእድሳት ምክንያት ንቃይ የእንጨት በሮች ፣ ንቃይ የመፀዳጃ ቤት በሮች ፣ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮች ፣ አሉሙኒየም በርና መስኮት ፣ ጠረጴዛዎች ፣ የወለል እምነበረድ እና የመሳሰሉት ለሽያጭ በድጋሚ በጨረታ ያቀረበ ስለሆነ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ

- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣
- የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በAudit Service Corporation ስም በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ብር 50 (ሃምሳ ብር) የማይመለስ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 710 በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ የስራ ቀን እና ሰዓት (ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር) ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍት ሆኖ የሚቆይ እና ጨረታው በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ላይ በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመቀበልም ሆነ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በአካል በመቅረብ የሚሸጠውን ንብረቶች በመመልከት የጨረታ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለመሳተፍ ከላይ የተመለከቱትንና ሌሎች ማስረጃዎች በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ አድራሻ ቂርቆስ ክ/ከ ካዛንችስ ከኦዳ ህንፃ (ሲንቄ ባንክ) ፊት ለፊት ወይም ከአይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልከ ቁጥር 0913601006 ወይም በ0913166504 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን