የደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማሽኖች ቁርጥራጭ ብረቶችና የተለያየ መጠን ያለው ፌሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ማሽኖች ቁርጥራጭ ብረቶችና የተለያየ መጠን ያለው ፌሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ግለሰብ ከሆኑ የቀበሌ ወይም ናሽናል መታወቂያ እንዲሁም የንግድ ድርጅት ከሆኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሠዓት ከጠዋቱ 2፡30-10:00 ድረስ እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ድረስ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ በመምጣት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎኘ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- አንድ ተጫራች በሁሉም ወይም በከፊል ወይም በአንድ እቃ ላይ መጫረት ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ10ኛው ቀን ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታውን ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ እንገልፃለን፡፡
- ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡- +251911388194/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
