ሲዳማ ኤልቶ የገ/ኅ/ሥራ ዩኒየን በ2016/17 ምርት ዘመን ያሰባሰበውን 11000 ኩንታል የምግብ በቆሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ኤልቶ የገ/ኅ/ሥራ ዩኒየን በ2016/17 ምርት ዘመን ያሰባሰበውን 11000 ኩንታል የምግብ በቆሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ፡-
- ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7 ቀናት ውስጥ መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በ8ኛው ቀን ከቀኑ 4-6 ሰዓት ባለው ጊዜ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው / በተገኙበት በ8ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- የበለጠ መረጃ ለማግኘት ፅ/ቤት ድረስ በአካል መቅረብ ይችላሉ።
አድራሻ፡- ሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፊት ለፊት
ሲዳማ ኤልቶ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተ
