የአገልግሎት መ/ቤታችን እ.ኤ.አ በ2025 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውል የ Microsoft 365 EI የተጠቃሚ ቁጥር 400፣ Microsoft 365 E3 የተጠቃሚ ቁጥር 100 እና Microsoft Teams Essential የተጠቃሚ ቁጥር 500 የአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ስተአ/001/2025
የአገልግሎት መ/ቤታችን እ.ኤ.አ በ2025 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውል የ Microsoft 365 EI የተጠቃሚ ቁጥር 400፣ Microsoft 365 E3 የተጠቃሚ ቁጥር 100 እና Microsoft Teams Essential የተጠቃሚ ቁጥር 500 የአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም የመንግሥት ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ፣ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣በጨረታ ለመሳተፍ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም የተ.እ.ታ. ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን፣ በብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ውል በመግባት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ሚካኤል ከሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና መ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመምጣትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ለ16 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት፣ ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ስራ ቀናት አይደሉም፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጥቅል ዋጋ 2 /ሁለት በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በE.E.D.E Refugees and Returnees Service ስም በተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ-ሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ፣ የአገልግሎቱን ዋጋ፣ በቀረበው ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ መሰረት የቴክኒክ ሰነድ እና እንዲሁም በጨረታ ሠነዱ የተዘረዘሩትን የብቃትና የልምድ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚያያዙ ማስረጃዎች በሙሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላበቃላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሠነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ከታች በተመለከተው አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሰራተኞች ክበብ ምድር ቤት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ፣ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የስልክ ቁጥር 09-97-23-66-31
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
