ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በኢንዱስትሪያችን ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮችን (ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በኢንዱስትሪያችን ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮችን (ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ሸልፍ) በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት አስራ አምስት ቀን (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዋጋ በማስገባት መወዳደር የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን።
ተወዳዳሪዎች ከታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፤
- ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚያቀርበው ዋጋ በታሸገ ፖስታ መሆኑን ማረጋገጥና በኢንዱስትሪው ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡ ፖስታው ላይ የባለቤቱ ፊርማ መፈረም ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ወይንም ፓስፖርት ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች ጨረታውን ለመወዳደር የ5000 ብር (አምስት ሺህ ብር) በባንክ ሲፒኦ ከጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋ ላይ ቅሬታ ካላቸው ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ቅሬታቸውን በጽሑፍ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከተገለጸው ቀን በኋላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን።
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በአስራ አምስተኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን ጠዋት 4:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች አለመገኘታቸው ጨረታውን ከመከፈት የማያግደው መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻ፤
ከመገናኛ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት አንበሳ ጋራዥ አጠገብ ሲሆን ስልክ ቁጥር 0118-59-22-86 በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ አዲስ አበባ
በኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
