የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ገላን ከአቃቂ ኬላ አለፍ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ውስጥ ያለውን የአገልግሎት ጊዜ ያለፈበትን NPS, NPSB, UREA እና DAP የአፈር ማደበሪያን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ገላን ከአቃቂ ኬላ አለፍ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ውስጥ ያለውን የአገልግሎት ጊዜ ያለፈበትን NPS, NPSB, UREA እና DAP የአፈር ማደበሪያን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ይህንን የአፈር ማዳበሪያውን መግዛት የሚፈልግ ተጫራች ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ ቀጥሎ ያሉ መስፈርቶችን በማሟላትና በአካል በመገኘት በተዘጋጀው ፎርም ላይ የአንዱን ኩንታል ዋጋ እና አጠቃላይ ዋጋ ሞልቶ በማስገባት መወዳደር የሚችል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቹ የአፈር ማዳበሪያን ለመግዛት ህጋዊ የታደሠ ንግድ ፈቃድ፤ የዓመቱን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚገልጽ መረጃ እና ቲን ሰርተፍኬት አያይዛዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቹ ለጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ የዋጋውን 10% በሲፒኦ ቢድ ቦንድ አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቹ ለጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 1000.00 (ብር አንድ ሺ) በፌዴሬሽናችን ሂሳብ ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000007339856 ገቢ በማድረግ ከስድተኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 12 ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል የጨረታ ሰነድ መግዛት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በድርጅታችን ዋና ቢሮ አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል ጎን በሚገኘው OACF Building ወይም የቀድሞ ኤክስፕሬስ ፕላዛ ህንጻ ስድስተኛ ፎቅ በአካል በመገኘት በተዘጋጀው ፎርም ላይ ዋጋ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 (ሃያ አንድ) ተከታተይ ቀናት ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሳጥን መዝጊያ ጨረታው በወጣበት በ21 (ሃያ አንደኛው) ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ8፡30 (በስምንት ሰዓት ተኩል) ይሆናል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ሆኖ በተመሳሳይ ሰዓትና ደቂቃ ላይ የሚዘጋ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥን መክፈቻ ቀን ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በ21 (ሃያ አንደኛዉ) ቀን የስራ ቀን ከሆነ በ9፡00 (በዘጠኝ ሰዓት) ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይሆናል፡፡ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ሆኖ በተመሳሳይ ሰዓትና ደቂቃ ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ በተባለው ጊዜ ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ እነሱ በሌሉበት የመክፈቻ ሂደቱ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች ወይም እኩል ዋጋ የሰጠ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች አንድ ተጫራች ባቀረበዉ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- አሸናፊው የገዛውን ንብረት ሙሉ ዋጋ በመክፈል በ10 (አስር) ቀን ውስጥ ከፌዴሬሽኑ መጋዘን ማንሳት ይኖርበታል፡፡
- ደርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- የጨረታው ውጤት የጨረታው ኮሚቴ አሸናፊውን ከለየ በኋላ በስልክ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
- የጨረታውን ሠነድ ያሸነፈ አካል የአፈር ማዳበሪያውን መልሶ ለአርሶ አደሩ ላለመሸጥ ድርጅቱ ያዘጋጀውን የግዴታ ውል መፈረም ፈቀደኛ የሆነ፡፡
አድራሻ፡- ድርጅታችን ዋና ቢሮ አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል ጎን በሚገኘው OACF Building ወይም የቀድሞ ኤክስፕሬስ ፕላዛ ህንፃ ስድስተኛ ፎቅ ላይ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ምርቱ የሚገኝበት ቦታ (የመጋዘን ሰራተኛ) 09 11 58 68 57/09 12 62 24 21/09 10 64 54 42 ወይም 09 13 45 61 10 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ
