የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ እንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለቀበሌ እንስሳት ክሊኒኮች ለእንሰሳት ህክምና አገልግሎት የሚውል መድሀኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ደ/ዙ/ዝና ግዥ /114/2017
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ እንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለቀበሌ እንስሳት ክሊኒኮች ለእንሰሳት ህክምና አገልግሎት የሚውል መድሀኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይ መሆን አለባቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አይይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ ከደሴ ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከ8/10 /2017 ዓ.ም እስከ 2/11/2017 ዓ.ም በአየር ላይ ይውላል።
- ጨረታው በ3/11/2017 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ኦርጅናል መድሀኒት መሙላትና ያሸነፉበትን መድሀኒት በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው።
- የሚገዙ መድሀኒቶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የመድሀኒት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚያቀርቡት መድሀኒት ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በጽ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት።
- ተሸናፊ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ያስያዙት 2% ሲ.ፒ.ኦ ከአምስት ቀን በኋላ ይመለስላቸዋል።
- አሸናፊው አካል የሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን መድሀኒት በራሱ ወጪ ለሴክተሩ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ እስከ 3/11 /2017 ዓ.ም ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ እንድያስገቡ እየገለፅን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-77-63 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- እያንዳንዳቸዉ መድሀኒት የጊዜ ቆይታ ሁለት አመትና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ድርጅት ተጫራች ኦርጅናል መድሀኒት የማቅረብ ግደታ አለባቸው።
የጨረታ መክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ወደ ሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይተላለፋል።
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
ስልክ 033 111 77 63 ይደውሉ።
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
