Tender Detail

Tender Details

  • Company በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል
  • Address ከሚሴ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 51 99 99 75
  • Website
  • Deadline12 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-07-12 00:00:00
  • Categories Furniture , Electronics Materials

በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ከጣልያን ፕሮጀክት ኮርፖሬሽን በተገኘ ድጋፍ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ከጣልያን ፕሮጀክት ኮርፖሬሽን በተገኘ ድጋፍ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በበጀት ዓመቱ (2017) . የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ /TIN/ ያላቸው፡፡
  2. የጨረታውን ሰነድ ከከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 50 በግዥ /ንብ/አስ/የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ.ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ ከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስተኛው /16ኛው ቀን ከጠዋቱ 300 ሰዓት እስከ 400 ሰዓት ድረስ ባለው ግዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን 430 ሰዓት ላይ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% / ሁለት ፐርሰንት/ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ትእዛዝ /CPO/ማስያዝ አለባቸው።
  6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ግዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  8. የዕቃው ርክክብ ቦታ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ይሆናል፡፡
  9. ውድድሩን በነጠላ ዋጋ የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  10. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 09 51 99 99 75 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

 

በአማራ /ክልላዊ መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል

 

Save Tender