ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን GPS ግዥ አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የGPS ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኅብኮን 23/2017
ኮርፖሬሽናችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለጸውን GPS ግዥ አቅራቢ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው ዕቃ አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
GPS የሚፈለግበት ፕሮጀክት |
ምርመራ |
|
1 |
GPS |
በቁጥር |
3 |
ለተለያዩ ፕሮጀክቶች |
|
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የተ.እ ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ቁጥር እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው የሚገልጽ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ሲፒ.ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል በኮርፖሬሽናችን ስም የተሰራ የባንክ ጋራንቲ የተ.እ.ታክስን ጨምሮ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ኮርፖሬሽናችን አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን የGPS መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተገለጸው የGPS አቅርቦት ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ ለብቻ እንዲሁም የዋጋ መሙያ ፋይናንሽያል ሰነድ ቅጅ እና ዋና ለየብቻ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያን በፖስታ በማሸግ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:10 ይከፈታል። ነገር ግን የመክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከኮርፖሬሽናችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-220-45-79 መደወል ይችላሉ።
ኅብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
ባ/ዳር
