የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ይዞታዎቹ ሊሰራ ላቀዳቸው ግንባታዎች የግንባታ ዲዛይን ስራ አገልግሎት ግዢ NCB 0017/2017 በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግንባታ ዲዛይን ስራ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB-0018/2017
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በሚገኙ ሁለት ይዞታዎቹ ሊሰራ ላቀዳቸው ግንባታዎች የግንባታ ዲዛይን ስራ አገልግሎት ግዢ NCB 0017/2017 በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበት መረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቲን ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ያሏቸው ለመሆኑ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 20,000.00 በባንክ በተመሰከረለት ቼክ፣ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ድረስ በመምጣት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋና የቴክኒክ መግለጫዎች አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጥቀስ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 5:45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል።
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 011-5-17-25-21/11 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
