የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮች ለመግዛት በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 የበጀት ዓመት:-
- የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ/ሥራ ለሁለተኛ ጊዜ ማሰራት
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለሁለተኛ ጊዜ እና
- የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ለሶስተኛ ጊዜ በመግዛት በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፋበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየ ብቻ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለው፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ እያንዳንዱ ጨረታ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ጨረታው የሚከፈተው በ11/111/2017 ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ15/11/2017 ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ/ሥራ ጨረታው የሚከፈተው በ15/11/2017 ከቀኑ 9፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ተጫራቾች የሚሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 10,000 (አስር ሺህ) ብር በCBE፣ CBO እና በSinqe" ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0228123956 ደውለው መረዳት ይችላሉ
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ
