የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል ማጣፈጫ በዘርፉ ከተሠማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ምግብ አገልግሎት የሚውል ማጣፈጫ በዘርፉ ከተሠማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የሚጠበቅባቸውን ወቅታዊ ግብር የከፈሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማጣፈጫ ለ6 ወራት የሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በየወሩ እስከ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለፁትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና፣ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተረጋገጠ CPO 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 15 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ15ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል። ይህ ቀን የበዓልም ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች የማጣፈጫ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ ኮሚቴ ማሳዬት አለበት፤-
- ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ) ብር በማይመለስ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር፡- 046-122-80-84 መደወል ይችላሉ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም
