የኦሮሚያ የግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ባለ 50 ኪሎዋት እና ባለ 100 ኪሎዋት ጀኔሬተር ግዥ በሰነድ ላይ ባለው መስፈርት መሰረት በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ የግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ባለ 50 ኪሎዋት እና ባለ 100 ኪሎዋት ጀኔሬተር ግዥ በሰነድ ላይ ባለው መስፈርት መሰረት በዘርፉ ላይ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን፤
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ የግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን ይህ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት ብቻ መውሰድ ይቻላል።
- ተጫራቾች በዚህ የንግድ ዘርፍ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ቲን፣ ቫት፣ የንግድ ምዝገባ እና ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ፣ ቼክ፣ ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የዋጋውን 5% (አምስት ፐርሰንት) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
- ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት
- ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በ22ኛው ቀን ከ4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በዚሁ እለት 4፡00 የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት 4፡30 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው መስፈርቶችን መሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 12
ስልክ:- 0910645442
የኦሮሚያ የግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን
