ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ኮን ግዳን ወረዳ ለሚገኙና የምግብ እጥረት ለታየባቸው ሕፃናት፣ ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች በድጋፍ መልክ የሚሰጥ ምግብ ነክ ግብአቶችን እንዲሁም በግዳን ወረዳ ለሚገኙ 4 የእንሰሳት ጤና ክሊኒኮች በድጋፍ መልክ የሚሰጥ የእንሰሳት መድሃኒትና የሕክምና ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች/ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ የምግብ ነክ ግብአቶች፣ የእንሰሳት መድሃኒትና የሕክምና ዕቃዎች ግዥ ጨረታ
ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት ከኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ኮን ግዳን ወረዳ ለሚገኙና የምግብ እጥረት ለታየባቸው ሕፃናት፣ ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች በድጋፍ መልክ የሚሰጥ ምግብ ነክ ግብአቶችን እንዲሁም በግዳን ወረዳ ለሚገኙ 4 የእንሰሳት ጤና ክሊኒኮች በድጋፍ መልክ የሚሰጥ የእንሰሳት መድሃኒትና የሕክምና ዕቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች/ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፎቹ የተሠማራችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ
- በበጀት ዓመቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸሁ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ቲን ቁጥር ስርተፍኬት ያላቸሁ፣
- በምትወዳደሩበት ዘርፍ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ድርጅቶች/ነጋዴዎች
ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 07 (ሰባት) ቀናት የጨረታ ሠነዱን በብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ቀይት ከሚገኙ የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከባንክ ሲፒኦ ጋር በፖስታ አሽጎ በማስገባት እንድትወዳደሩ እየጋበዝን ጨረታው በ8ኛው ቀን በ4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሠዓት የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን 8ኛዉ ቀን በካላንደር የሚዘጋ በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት
ደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር
ጣይቱ ክፍለ ከተማ ቀይት ቀበሌ
ለተጨማሪ መረጃ
ስ.ቁ 011-656-0249 ወይም
ኢሜል: procurement@tesfab.org