የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ለ2017/18 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ውስጥ የተዘረዘሩትን የስፖርት እና የምግብ አቅርቦት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአትሌቶች የስፖርት ትጥቅ እና የምግብ አቅርቦት ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፣ ኦ.ደ.ዱ.እ.ድ - 02/2018
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ለ2017/18 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሰንጠረዡ ውስጥ የተዘረዘሩትን የስፖርት እና የምግብ አቅርቦት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት |
ዝርዝር መግለጫ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1. |
የአትሌቶች የስፖርት ትጥቅ |
የተለያየ |
የቦርድ አባላትን አካቶ ለ54 ሰው |
100,00.00 |
|
2. |
የአትሌቶች የምግብ አቅርቦት |
ቁጥር |
እስከ 46 ለሚደርሱ አትሌቶች |
50,000.00 |
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉና በዘርፉ የተሰማሩትን ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው ላይ በሙሉም ሆነ በከፈል እንዲሳተፉ መ/ቤቱ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ በጨረታ ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል፣ አዲስ አበባ ከተማ ቀበና ኦይል ሊቢያ አጠገብ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት፤ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በማየት እያንዳንዱን ዕቃ የሚያቀርብበትን ዋጋ በመሙላት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,00.00 (አንድ መቶ ሺህ) ለሎት1፣ 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ለሎት 2 ከታወቀ ባንከ በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ስም ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንከ ዋስትና (Bank Guarantee) በማሠራት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብና ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ጨረታው ነሐሴ 26 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለጸው አድራሻ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ናሙና ለተጠየቀላቸው ዕቃዎች ናሙና ይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ተማረች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም:
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ከታች የተገስጸውን ስልክ ቁጥር በመደወል ወይም በፋክስ በጽሁፍ በመጠየቅ ማብራሪያ ማሣኘት ይችላሉ።
አድራሻ:- አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ አራዳ ክ/ከተማ፤ ወረዳ 07
ስልክ ቁ. 011 122 0020 / 011 124 0258 ይደውሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
