Tender Detail

Tender Details

  • Company በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 7 ሰኔ ዘጠኝ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት
  • Address በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ከካዲስኮ ወረድ ብሎ በሚገኘው ቴሌ ኮሚኒኬሽን ወደ ቀኝ በሚያስገባው መንገድ 400 ሜትር ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-8-88-29-10
  • Website
  • Deadline09 Sep 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 300 /ሶስት መቶ ብር/
  • opening dateበ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Sport Materials And Sportswear

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 7 የሠኔ ዘጠኝ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መስያ ቁጥር 01/2018

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 7 የሠኔ ዘጠኝ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን

ሎት 1 የደንብ ልብስ 38250
ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች 23254.50
ሎት 3 የት/ት መርጃ እቃዎች 5250
ሎት 4 የፅዳት እቃዎች 28062.72
ሎት 5 የጥገና እቃዎች 13000
ሎት 6 የእስፖርት እቃዎች 5250
ሎት 7 የህከምና የመ/እርዳታ መስጫ 900
ሎት 8 ቋሚ እቃዎች 16500

ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል በዚሁ መሰረት :-

በጨረታው ለመወዳደር ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ ተጫራቾች አምራችነታችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል

  1. ተጫራቾች በየሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  2. ተጫራቾች ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከ/ከተማ ሰኔ 9 የመ/ደ/ት ቤት የፋ/ግ/ን ደጋፊ የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 05 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ በማስቀመጥ የግዥውን አይነት በመጥቀስ እና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ተኩል ታሽጐ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በት/ቤቱ የፋ/ግ/ን/ደጋፊ የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የባዕል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በተያያዘው የፍላጐት መግለጫ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
  6. የዘገየ ተጫራችና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ አለው ነው፡፡
  9. መ/ቤቱ የሚያጫርተውን እቃ ብዛት እንደአስፈላጊነቱ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ በድጋሚ ማዘዝ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች ላሸነፉት ለቋሚ እቃ የአንድ ዓመት ዋስትና መስጠት ይኖርባቸዋል፤

ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ

አድራሻ፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ከካዲስኮ ወረድ ብሎ በሚገኘው ቴሌኮሚኒኬሽን ወደ ቀኝ በሚያስገባው መንገድ 400 ሜትር ላይ ሲሆን የመ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 011 8 88 29 10

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 7 የሠኔ ዘጠኝ የመጀ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for supplying uniforms, office supplies, teaching aids, cleaning materials, maintenance items, sports equipment, medical/first aid supplies, and fixed assets across 8 lots. Bidders must hold valid licenses, pay taxes, and be registered for TIN/VAT. Samples required for lots 1–7.
Save Tender