የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/UF/114/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የዕቃው ዓይነት
|
የፕሮጀክት ስም
|
የጨረታ ቁጥር
|
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት
|
የጨረታ መከፈቻ ቀን እና ሰዓት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1
|
የደንብ ልብስ
|
ዋና መ/ቤት
|
DCE/UF/114/2026
|
መስከረም 06/2019 ዓ.ም4፡00 ሰዓት
|
መስከረም 06/2019 ዓ.ም4፡15 ሰዓት
|
50,000.00
|
ስለሆነም፡
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ…ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚያቀርቡበት ወቅት ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች አብሮ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114 40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
