የአዳማ ከተማ አትሌቲክስ ክለብ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓ.ም የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ አትሌቲክስ ክለብ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓ.ም የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ተወዳዳሪዎች ሟሟላት ያለባቸው መስፈርቶች /የተጫራቾች መመሪያ/፡:
-
- ማንኛውም ድርጅት ግለሰብ እና በዘርፉ የተሰማሩ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የገበረ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ቫት /vat/ ተመዝጋቢ እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል አዳማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሲንቄ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1054551161211 በማስገባት ጨረታው ከወጣቦት የስራ ቀን ጀምሮ አዳማ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለምግብ አቅርቦት 50,000.00 /ሃምሳ ሺ/ ብር በባንክ ቼክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀን የሚቆይ ሆኖ በ 16ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም ሆኖም 16ኛው ስራ ቀን በዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻልን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒውን እና ኦርጅናሉን በተናጠል በማቅረብ አዳማ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ጽ/ቤት በመቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን ማስገባት ይችላል፡፡
- ለአትሌቲክስ ክለብ በአሰላ ካምፕ ለ100 አትሌቶች መመገብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ለአትሌቶች ምግብ በሚዘጋጅበት አዳራሽ ውስጥ ከአልኮል መጠጥ፣ ከተለያዩ ሱስ አስያዥ፤ ዕፆች የራቀ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በቂ የማዕድ ቤት እና የምግብ ቁሳቁስ ከበቂ የሰው ሃይል ጋር ያለው መሆን ይጠበቅበታል።
- ተጫራቾች በ2017 ዓ.ም በዚህ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ መሆኑን የሚገልፅ የስራ ልምድ ከንግድ እና ገበያ አገልግሎት ፅ/ቤት እና ሲሰሩ ከነበረበት ቦታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0223311250/0912488327
የአዳማ ከተማ አትሌቲክስ ክለብ
