ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኙ ለኮምቦልቻ እና መልጌ ወንዶ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች እንዲሁም ለደ/ዘይት ቄራ ለእርድ አገልግሎት የሚያስፈልጉ እና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቀርቡ ወንድ የዳልጋ ከብቶችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ከሚችሉ ልምድና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር EL/LP-03/2025
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኙ ለኮምቦልቻ እና መልጌ ወንዶ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች እንዲሁም ለደ/ዘይት ቄራ ለእርድ አገልግሎት የሚያስፈልጉ እና ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቀርቡ ወንድ የዳልጋ ከብቶችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ከሚችሉ ልምድና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የቁመና ክብደታቸውም ኮምቦልቻ ምግብ ማቀነባበሪያ የሚያስፈልጉ ከብቶች፡-
- የቁመና ክብደታቸው 170-199 ኪ.ግ እና በላይ የሆኑና ያልተጣራ የስጋ ምርታቸው 27% ብዛታቸው 3270 በሳምንት 136
- የቁመና ክብደታቸው 200-224 ኪ.ግ እና በላይ የሆኑና ያልተጣራ የስጋ ምርታቸው 30% ብዛታቸው 3270 በሳምንት 136
- የቁመና ክብደታቸው ከ225 ኪግ እና በላይ የሆኑና ያልተጣራ የስጋ ምርታቸው 33% ብዛታቸው 3270 በሳምንት 136 በአጠቃላይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት 9810 ከብቶችን ለማቅረብ የሚችሉ እና ሙሉ የስጋ ይዘት ያላቸው፣ ያልከሱ በቆዳቸው ላይ ጉዳት (ጠባሳ) የሌላቸው የርክክብ ሂደቱ ባለሙያዎች በሚያወጡት መስፈረት መሆን አለባቸው።
እንዲሁም ለመልጌ ወንዶ ምግብ ማቀነባበሪያ የሚያስፈልጉ ከብቶች፡-
- የቁመና ከብደታቸው 170-199 ኪ.ግ እና በላይ የሆኑና ያልተጣራ የስጋ ምርታቸው 27% ብዛታቸው 785 በሳምንት 32
- የቁመና ክብደታቸው 200-224 ኪግ እና በላይ የሆኑና ያልተጣራ የስጋ ምርታቸው 30% ብዛታቸው 2355 በሳምንት 98
- የቁመና ክብደታቸው ከ225 ኪ.ግ እና በላይ የሆኑና ያልተጣራ የስጋ ምርታቸው 33% ብዛታቸው 785 በሳምንት 32 በአጠቃላይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት 3925 ከብቶችን ለማቅረብ የሚችሉ እና ሙሉ የስጋ ይዘት ያላቸው ያልከሱ በቆዳቸው ላይ ጉዳት (ጠባሳ) የሌላቸው የርክክብ ሂደቱ ባለሙያዎች በሚያወጡት መስፈርት መሆን አለባቸው።
በተጨማሪ ለቢሾፍቱ ቄራ የሚያስፈልጉ ከብቶች፡-
- የቁመና ክብደታቸው ከ225 ኪ.ግ እና በላይ የሆኑና ያልተጣራ የስጋ ምርታቸው 33% ሆኖ 50% ከነአጥንቱ ብዛታቸው 1190 በሳምንት 49 በአጠቃላይ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት 1190 ከብቶችን ለማቅረብ የሚችሉ እና ሙሉ የስጋ ይዘት ያላቸው ያልከሱ በቆዳቸው ላይ ጉዳት (ጠባሳ) የሌላቸው የርክክብ ሂደቱ ባለሙያዎች በሚያወጡት መስፈርት መሆን አለባቸው።
ማሳሰቢያ፡-
- ለኮምቦልቻ እና መልጊ ወንዶ ላሉት አቅርቦቶች ወንድ የዳልጋ ከብቶች ሲሆኑ እንዲሁም ሴት የዳልጋ ከብቶች የሚቀርቡ ከሆና በግብርና ሚኒስቴር መመሪያ ቁጥር 13/54/1/11 በቀን 12/02/2014 ዓ.ም መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡
- ለቢሾፍቱ ቄራ አቅርቦቶች ወንድ የዳልጋ ከብቶች ብቻ ይሆናል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከማህበራት ውጪ ያሉት ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ተርን ኦቨር ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚመለስ ብር ለእያንዳንዱ ምድብ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ጠቅላላ ካሸነፈው አቅርቦት ክፍያ ተመመጣኝ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው እና በተያያዘው የአቅርቦትና የጥራት መሥፈርት መሠረት ጨረታውን መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ ዓርብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ቅዳሜ እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ላም በረት አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ አቅርቦት መምሪያ ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ 200.00 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሰነዳቸውን እስከ መስከረም 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላምበረት በሚገኘው አዲሱ የኤልፎራ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ በሚገኘው ይከፈትና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 116461076 /0911867645/251911625992 /0927718699 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር
