የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አ/ማኅበር ከስሩ የተዘረዘሩት ያገለገሉ ንቃይ እቃዎች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አ/ማኅበር ከስሩ የተዘረዘሩት ያገለገሉ ንቃይ እቃዎች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የእቃዎቹ ዝርዝር እንደሚከተለው ነው
- የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶች በኪሎ የሚገዙበትን ዋጋ
- የሽንት ቤት መቀመጫዎች ብዛት 69 የሚዝዙበትን ዋጋ
- የቁም መሽኛ ሲንኮች በቁጥር 9 የሚገዙበትን ዋጋ
- ሻታፍ ብዛት 19 የሚገዙበትን ዋጋ
- እጅ መታጠቢያ ሲንክ ከነ መሸከሚያው በቁጥር 25 የሚገዙበትን ዋጋ
- የፊት መስታወት በቁጥር 14 የሚገዙበትን ዋጋ
- የሶፍት ማስቀመጪያ በቁጥር 37 የሚገዙበትን ዋጋ
- ንቃይ አልሙኒየም በሮች በቁጥር 52 የሚገዙበትን ዋጋ
- ንቃይ አልሙኒየም በሮች መስታወት የሌላቸው ፍሬም ብቻ በቁጥር 14 የሚገዙበትን ዋጋ
- ትልልቅ የሻተር ንቃይ በሮች በቁጥር 2 የሚገዙበትን ዋጋ
- የኮርኒስ ፒ.ፒ.ሲ በቁጥር 6 እስር የሚገዙበትን ዋጋ
- የተወረሱ ሀገርኛ ቦርሳዎች ብዛት ከ116 ትንንሽ የሚገዙበትን ዋጋ እና
- የተወረሱ ሀገርኛ ቦርሳዎች ብዛት 114 ትልልቅ የሚገዙበትን ዋጋ
- ቁርጥራጭና ንቃይ እንጨቶች ባለበት ሁኔታ የሚገዙበት ዋጋ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የሚወገዱ እቃዎች የሚገዙበትን ዋጋ እና ለጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ የብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በማሰራት ከሰነዱ ጋር በታሸገ ፖስታ ከመስከረም 02 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ድረስ ሆኖ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ 7፡30 ብቻ ማስገባት ይቻላል፡፡
የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 200 በኢትዮጵያ ንገድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000157339129 በማስገባት ባንክ ስሊፕ በማቅረብ ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የእሴት ታክስ (ቫት)
ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ 7፡30 ብቻ ማስገባት የሚቻልና በዛው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ -
ለጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ የብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
ጨረታውን ያሸነፈ ሰው ንብረቱን በ3 ቀናት ማንሳት አለበት
የጨረታ ተሸናፊ ያስያዘው ገንዘብ በማግስቱ ይመለስለታል፡፡
እቃው አ/ማኅበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ ማየት ይቻላል፡፡
አ/ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ኮልፌ አጠና ተራ የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አ/ማኅበር
ብሎክ-2 ቢሮ ቁጥር 4
ስልክ 0963371045/0932080377
የኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ሕይወት አ/ማኅበር
