የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃ.የተ በገላን ከተማ ከአቃቂ ኬላ አለፍ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ውስጥ ያለውን የአገልግሎት ጊዜ ያለፈበትን NPS, NPSB, UREA እና DAP የአፈር ማዳበሪያን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ አፈር ማዳበሪያ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፈዴሬሽን ኃ.የተ በገላን ከተማ ከአቃቂ ኬላ አለፍ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ውስጥ ያለውን የአገልግሎት ጊዜ ያለፈበትን NPS, NPSB, UREA እና DAP የአፈር ማዳበሪያን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል።
- ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የቫት፣ የቲን ቁጥር ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000.00 (እንድ ሺህ ብር) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኦሮሚያ ግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ.የተ አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACE ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦ/ግ/ህ/ሥ/ማ/ፈ የግዥ ክፍል በመገኘት ይህ ጨረታ ማስታውቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11 ተከታታይ ቀናት ብቻ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የ90 ቀን ዋስትና ያለው ቢድ ቦንድ፣ ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር የዋጋውን 5% (አምስት ፐርሰንት) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
- የጨረታው አሸናፈ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከድርጅቱ ጋር ውል በመፈጸም እና የዋጋውን 10% (አስር ፐርሰንት) የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ እና ገንዘቡን ከፍሎ ንብረቱን ማንሳት አለበት። በተጠቀሰው ቀን ውስጥ ካላነሱ የጨረታው አሸናፊ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለኦ/ግ/ሕ/ሥ/ማ ፈዴሬሽን ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ ገላን ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በመገኘት ንብረቱን በስራ ሰዓት መመልከት ይችላል።
- ጨረታው የሚገባበት እና የሚከፈትበት
- ተጫራቾች የሚዝዙበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በ12ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በዚሁ እለት 4፡00 የሚዘጋ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት በ4፡30 ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- የመወዳደሪያ መስፈርቶችን ሙሉ ለሙሉ ላሟሉ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ታይቶ አሸናፊው ተጫራች የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ለተሸነፉት ተጫራቾች ከውድድሩ ውጤት በኋላ የሚመለስ ሲሆን ያሸነፈ ተጫራች ግን ንብረቱን በተባለው ጊዜ ገደብ ውስጥ ካነሳ ብቻ የሚመለስ ይሆናል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: አዲስ አበባ ጀሞ ሚካኤል አደባባይ ሚካኤል ቤ/ክ ጎን OACF ህንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር፡ 0910645442
የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ
