የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ ዕቃ ግዥ (አገልግሎት) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ ዕቃ ግዥ (አገልግሎት) ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም፡- በድጋሚ ጨረታ የሚወጡ የዕቃ /የአገልግሱት/ ግዥ
ሎት 1 - ለቨርችዋል ባንኪንግ የሚሆን ቦታ ኪራይ፤
ሎት 2 - የጤፍ እና የሩዝ አቅርቦት ግዥ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላትና ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም /የ2018 ዓ.ም/ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ TIN እና VAT ሰርተፊኬት ያላቸው፤ የነቢዎች ከሊራንስና በጨረታ ለመሳተፍ ከሃገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ለቨርችዋል ባንኪንግ አገልግሎት ለመስጠት ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ፈቃድና የተመዘገቡበት የቅርብ ጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 የግዥ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ለሎት 2 ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት ቡድን መሪ ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከሻት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም፡፡ ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፣ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት፡፡ ስለዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
7. ጨረታን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሽንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል፡፡
8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር በመጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም እስከ 20% በመቀነስ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
9. ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 00:8
10. ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴከኒካል ሰነድ እና ፋይናሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ /Bid Document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታ ቴከኒካል ፕሮፖዛል ሰነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ማስገባ አለባቸው፡፡
11. የጨረታ ሂደቱ የቴከኒክ ግምግማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለሎት 1 ቴክኒካል ሰነድ ግምግማ ውጤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) እንዲሁም ለሎት 2 ናሙና ጥራት እና ድርጅታዊ ብቃት ውጤት (60%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ (40%) ሲሆን በድምር ውጤት አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ቴከኒካል ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሻል እንደማይከፈት እንዲታወቅ፡፡ የመገምገሚያ መስፈርቶቹ በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ማየት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 011-5-53-07-67/011-5-15-73-370
ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት
