በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የቤዛዊት ሸኔልሆም የህንፃ ተገጣጣሚ አካላት ማምረቻ ፋብሪካ ከኛ ኀልስን ሥራ የሚያገለግል ኤሌክትሪካል ሚክሰር ፓምፕ/Mini Avant piston pump/፤ 2ኛ ፓኔል እሴምብሊንግ ማሽን፤ 3ኛ ዋየር ስትሬቲንግ (R6) ማሽን እና የፋብሪካ ስፔር ፓርት (መለዋወጫ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሕጋዊ ከሆነው አሸናፊ ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የቤዛዊት ሸኔልሆም የህንፃ ተገጣጣሚ አካላት ማምረቻ ፋብሪካ ከኛ ኀልስን ሥራ የሚያገለግል ኤሌክትሪካል ሚክሰር ፓምፕ/Mini Avant piston pump/፤ 2ኛ ፓኔል እሴምብሊንግ ማሽን፤ 3ኛ ዋየር ስትሬቲንግ (R6) ማሽን እና የፋብሪካ ስፔር ፓርት (መለዋወጫ) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሕጋዊ ከሆነው አሸናፊ ድርጅት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ዝርዝር መረጃው በሰነዱ ተካቷል፤ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
-
በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጫራቶች በጨረታ ወቅት ዋናውን እና ቅጅውን ለይተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN /የግዥው/የሽያጩ /መጠን ብር 200,000.00/ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ/ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
የጨረታ ሰነዱን በባሕር ዳር በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የቤዛዊት ሸኔልሆም የሕንፃ ተገጣጣሚ አካላት ማምረቻ ፋብሪካ በአካል በመቅረብ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከመስከረም 18 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
-
የጨረታ አሸናፊው ለአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ሥራ አፈፃፃም ዋስትና /ፕርፎርማንስ ቦንድ/ በCPO ማስያዝ አለበት፡፡
-
የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት ተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
-
ፋብሪካው የጨረታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር እንዳስፈላጊነቱ ሊጨምር ይችላል፡፡
-
የመክፈቻ ቀኑ የካላንደር (የበዓል ቀን) ዝግ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
-
ለተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 05 83 21 09 20 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
-
አድራሻ፦ ባሕር ዳር አፄ-ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አሽርፍ ኢንዱስትሪ 100 ሜትር ገባ ብሎ ጣና ሞባይል ጎን በሚገኘው ፋብሪካ ነው፡፡
በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የቤዛዊት ሸኔልሆም የህንፃ ተገጣጣሚ አካላት ማምረቻ ፋብሪካ
