የኢትዮጵያ ፖስታ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሰውን የፕሮሞሽን ማስታወቂያ ስራ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግጨ 05/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፖስታ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሰውን የፕሮሞሽን ማስታወቂያ ስራ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
ሠንጠረዥ 1 ግዥ የሚፈፀምበት የጨረታ አይነቶች
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የጨረታ አይነት |
ብዛት |
ሰነዱ የሚመለስበት የመጨረሻው ቀን |
የመክፈቻ ቀን |
|
1. |
|
የፕሮሞሽን ማስታወቂያ ስራ |
|
ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት |
ጥቅምት 12/2018 ዓ/ም ከሰዓት 8፡30 ላይ ይከፈታል |
ስለሆነም፡- በዚህ ጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በድርጅቱ ገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል እየቀረቡ የጨረታ ሠነድ በመውሰድ
- ለሎት 1 ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ (በተናጠል) በጨረታ ሠነዱ ላይ በዝርዝር በተገለጸው የስራ ዝርዝር (specification) መሠረት ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ሠነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ኤንቨሎፕ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የሠራተኞች ክበብ ይከፈታል።
- CPO (ሲፒኦ) ሲያሠሩ፡- "የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት" ወይም ETHIOPIAN POSTAL SERVICE ENTERPRISE በማለት ያሰሩ
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር /09-91-18-75-13/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ፖስታ
