በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጄት ፈርኒቸር (VIP) ዕቃ ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 05/2018
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጄት ፈርኒቸር (VIP) ዕቃ ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-
1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::
2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ርዳይሬከቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው።
3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
5 የእቃዎች የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ )ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
6. የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ ፖስታ አሽገው በአንድ እናት ማቅርብ አለባቸው። ጨረታው ቴክኒካልና ፋይናንሻል በአንድ ላይ ይከፈታል።
7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ 90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ብር ብቻ በሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል ባንከ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው።
8. ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
9. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ርዳይሬከቶሬት ቢሮ ማግኘት ይቻላል።
10. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሣሰቢያ – ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% -ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን።ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 046-221-7002/3
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
ሀዋሳ
