በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ በስሩ ለሚገኘው መድኃኒት ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሰው መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ 001/2018
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ በስሩ ለሚገኘው መድኃኒት ቤት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሰው መድኃኒቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
-
ተጫራቶች: - የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘርፉ አግባብ ያለውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን/ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ተያያዥ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በኢትዮጵያ በታወቀ ባንከ የተመሰከረለት የብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ) CPO በድርጅቱ ትክከለኛ ስም ላኮመንዛ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ በማሠራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈርመው ወኪል ከሆነ ከሚመለከተው ውክልና ሰጭ (መዝጋቢ እካል) የተሰጠ ሕጋዊ የውከልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
-
ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት ዋናና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ የተጫራቹ ድርጅት ማህተም ተደርጎበትና ተፈርሞ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ በሎክ 20 ቢሮ ቁጥር 2023 በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ አስ/ፋይ/አገ /ዘርፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ለዓት ድረስ ብቻ ማስገባት አለባቸው፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው ቀን እና ቢሮ ከጠዋቱ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፤ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
-
ተጫራቾች ባይገኙም ሰነዳቸው የተሟላ ሆኖ ከተገኘ በሌሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
-
ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ተጫራቾች አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን ዕቃ የኢንተርፕራይዙ ንብረት ክፍል የሚገኝበት ወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ካምፓስ ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች አሽናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በኢትዮጵያ በታወቀ ባንከ የተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
አሸናፊ ተጫራች በውሉ ውስጥ የተካተቱትን ሕጎች ማከበር አለባቸው፡፡
-
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0970750336 መጠቀም ይችላሉ
በወሎ ዩኒቨርሲቲ የላኮመንዛ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ
