Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብ/ክ/መ/ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ
  • Address ከሀዋሳ ገብርኤል ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-2-21-70-14
  • Website
  • Deadline13 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2025-11-13 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Sewerage , Contractors

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በአርበጎና ወረዳ ያዬ ከተማ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት ለማሰራት Lot RM3/18 እና Lot RM5/18 (Cooble stone Road With masonary Drainage work) ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ በአርበጎና ወረዳ ያዬ ከተማ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ በ2018 በጀት ዓመት ለማሰራት Lot RM3/18 እና Lot RM5/18 (Cooble stone Road With masonary Drainage work) ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

  1. ለሚሰራ የኮብልስቶንና የነርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ ሥራ ደረጃቸው GC -5 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮች 2018 በጀት ዓመት ፈቃዳቸው ያደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ አግባብነት ካለው መንግሥት ተቋም (በፈዴራል እና በሲዳማ ክልል) የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተጋቢ መሆን አለባቸው
  2. ስፈለጊ የግንባታ ማቴሪያሎች የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶች በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ አለባቸው
  3. በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ፕሮጀከት ሰርተው ለማስረከብ ከአሰሪና ከሚመለከታቸው መስራያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገበተው በሥራ ወቅት ከአሰሪ /ቤት ወይም ከአማካሪ /ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ኮንትራክተሮች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. በገባው ውል መሰረት ፕሮጀክት ሰርቶ ያስረከበ ተቋራጭና የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ድርጅቱ ለውድድር ያቀረበው ብታት (ቴክኒ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርተው ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳ ትክክለኛ ካልሆነ ድርጅቱ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ ማስከሪያ (bid security) የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ከጨረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያና ደንብ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውንና ተእታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፊኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የተለያዩ ከተማ የኮብልስቶንና የጎርፍ መውረጃ ቦይ ግንባታ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ በመፈል ሰነዱ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  8. አንድ ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መወዳደርም ሆነ የጨረታ ሠነዱን መግዛት አይችልም፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች ከጨረታው ዝጊ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው
  10. የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ፋይናንሺያል (ኦሪጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች እንዲሁም የቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) ሁለት ሁለት ኮፒዎች በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክሜንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተኛው ቀናት ከጠዋቱ 400 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ አስተዳደር ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ውይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ 600 ሰዓት ላይ ተዘግተው ከቀኑ 800 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ፈት አያግደውም
  12. ጨረታው ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ከአስር ፐርሰንት (10%) በላይ የዋጋ ቅናሽ (Rebate) የተደረገ ከሆነ ድርጅቱ ቀጥታ ከጨረታ ወድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  13. አሠሪ /ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  14. የጨረታው መግቢያና መከፈቻ ቀን የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር- 046-2-12-43-56

 

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ

 

Save Tender