የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ እና ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ እና ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት/ፕሮጀክት አድራሻ
|
የንብረት/ፕሮጀክት ዝርዝር
|
የቦታ ስፋት(በሄክታር) |
የጨረታ ሁኔታ |
የጨረታ ደረጃ |
ጨረታ
|
|
1 |
ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ |
አማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ 09 ቀበሌ
|
የጫማ እና የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ (በ ትግበራ ላይ ያለ) የህንፃ ግንባታዎች፣ ማሸነሪዎች እና የኤሌክትሪክ ሥራዎች |
6.83 ሄክታር |
ዝግ |
ሁለተኛ |
ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት |
|
2 |
አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም |
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 ቀበሌ 11 |
ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፤ የህንፃ ግንባታዎች፣የኤሌክትሪክ ስራዎች፣ ማሸነሪዎች፣ ቁሳ ቁሶች፣የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃ የምርት ከምችት
|
1678 ካሬ ሜትር በሊዝ የተገኘ መሬት |
ድርድር |
አንደኛ |
ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ፥
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ ለኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ፋብሪካ እስከ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ እና ለቆርቆሮ ፋብሪካ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከ4፡00-6:00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርበው መደራደር ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንከ ከፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.አ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ(ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውከልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. 15% የተጨማሪ እሴት ታከስና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ከፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ከፍያን ጨምሮ ገዥው ይከፍላል፡፡
6. አንዳንድ የድርጅቶቹ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ/ታክስ ለመንግስት ለመክፈል ይገደዳል፡፡
7. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን በፊት መጎብኘት ይችላሉ፡፡
8. የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል፡፡
9. ባንኩ ንብረቶቹን የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል፡፡
10. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ዋና መ/ቤት ታወርሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011--524-53-73/ 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡ የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬከቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፡፡
11.ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
