የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ለግንባታ፣ ዲዛይንና ማማከር ድርጅትና የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽን አቻ የሀብት ግመታ ጥናት እና ለህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽንና ለሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የቢዝነስ ሞዴል ጥናት ማስጠናት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር የመ/ል/ድ/አስ/ባለ/ግ/ ጨረታ 001/2018
የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ለግንባታ፣ ዲዛይንና ማማከር ድርጅትና የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽን አቻ የሀብት ግመታ ጥናት እና ለህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽንና ለሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የቢዝነስ ሞዴል ጥናት ማስጠናት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1- የአዲስ አበባ ከተማ የግንባታ፣ ዲዛይንና ማማከር ድርጅት አቻ የሀብት ግመታ ጥናት፤
- ሎት 2- የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽን አቻ የሀብት ግመታ ጥናት፤
- ሎት 3- የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችና ፓርኮች ኮርፖሬሽን የቢዝነስ ሞዴል ጥናት፤
- ሎት 4- የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የቢዝነስ ሞዴል ጥናት፤
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በፋይናንስ ቢሮ ዌብሳይት በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታች በዝርዝር በተቀመጠው መሰረት በየሎቱ በCPO ማስያዝ አለባቸው።
- ሎት 1. ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/
- ሎት 2. ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/
- ሎት 3. ብር 15,000.00 / አስራ አምስት ሺህ ብር/
- ሎት 4. ብር 10,000.00 / አስር ሺህ ብር/
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው መሆን አለባቸው። የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱን ሲገለፅለት ያሸነፈበትን ከጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ፒያሳ ከሚገኘው ዋስትና የንግድ ማእከል ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8/03 የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዋናውን እና ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዛኑ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በሌሉበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ፖስታ ተቀባይነት ያለውም።
አድራሻ፡- ፒያሳ የሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ህንፃ 8ኛ ፎቅ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን
ለበለጠ መረጃ - በስልክ ቁጥር 0111124485
የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን
