በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የተለያየ አይነት የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ:- PPPDS/NCB/003/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የተለያየ አይነት የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
No |
Description |
Amount OF Bid Security in ETB |
|
1 |
Different type of office furniture |
600,000.00 |
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
2. የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤..
3. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት/Tin Number/ ያላቸው፤
5. ግብር ስለመከፈላቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
6. ማንኛውም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን በማቅረብ ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ሆሳዕና በሚገኘው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ/ ብር በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
7. የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው 15ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የግዥና ዋጋ ጥናት ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
9. ጨረታው አየር ላይ መቆያው ጊዜ ባበቃበት ቀን 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች
ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
10. የጨረታ ማስታወቂያው የሚውልበት የመጨረሻ ቀን በዓል፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚውል ከሆነ
በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 09-10-92-89-86 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት
ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት
