ፐብሊከ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 003/2018 ዓ.ም
ፐብሊከ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎትı የአቴንዳንስ ማሽን፤
ሎት2 የዳታ ሴንተር ማቀዝቀዣ (Air Conditioner for Data Center) ሎት3) ሴፍቲ ጫማ(Safty Shoe)፤
-
ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የሥራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በማዘጋጀትና በኤንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል፡፡የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡-የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜከሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው፤ ስተጨማሪ መረጃ፦ስልክ ቁጥር -011-5-50-45-64
የፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
