የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የደህንነት እና የሥራ ጫማዎች ግዥ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ፌቤኮ/ብግጨ/ዕግ/22/11/18
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች የደንብ ልብስ እና የደህንነት እና የሥራ ጫማዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤኮ/ብግጨ/09/22/11/18 በ 3(ሦስት) ሎት ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የዕቃውን ዋጋ በአንድ የታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ የእቃ አይነት ናሙና ከጨረታ መክፈቻ ቀን 3 (ሶስት) ቀን አስቀድሞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
| ሎት | የዕቃ ዝርዝር | የጨረታ ማስከበሪያ |
| 1 | የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች (ሄልሜት እንፀባራቂ፣መነፅር እና ተዛማጅ እቃዎች) | 30,000.00 |
| 2 | የደንብ ልብስ (ሙሉ ልብስ፣ ሸሚዝ ቱታ፤ጋወን እና ተዛማጅ እቃዎች) | 50,000.00 |
| 3 | የደህንነት እና የሥራ ጫማዎች | 30,000.00 |
- ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊከ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃጸም መመሪያ 1070/2017 መሠረት ሲሆን ተጫራቾች ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው የኮርፓሬሽኑ ዋና መ/ቤት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር201 ለዚሁ አገልግሎት ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ወይም ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንከ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መከፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ዌብሳይት Website www.fhc.gov.et የፖ.ሣ.ቁ P.O. Box 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
✨ messages.ai_summary
- The Federal Housing Corporation is procuring safety protective items (Lot 1), uniforms and related clothing (Lot 2), and safety and work shoes (Lot 3) through an open tender in Addis Ababa.
- Bid document price: 500 ETB (non-refundable). Bid bonds: 30,000 ETB (Lot 1), 50,000 ETB (Lot 2), and 30,000 ETB (Lot 3), payable via bank guarantee or CPO.
- Submission deadline: Nehase 26, 2018 E.C. at 4:00 AM; opening is the same day at 4:15 AM. Samples must be submitted 3 days before the opening date.
- Bidders must hold a renewed business license and provide tax clearance evidence.
