በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩከ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ እና በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩከ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ
የተለያዩ ኮስሞቲክስ ዘርፍ እቃዎች፣ አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ እቃዎች፣ ስፔር ፓርት ዘርፍ እቃዎች እና ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች በግልፅ ጨረታ
እንዲሁም አልባሳት ዘርፍ እቃዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች እና ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች በሐራጅ ጨረታ በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/209 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. በጨረታው ሸያጭ ስርዓት ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የጸና የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ያለበት ሲሆን በሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከላይ የተጠየቁትን መረጃዎች በጨረታ መክፈቻ ቀን ይዘው መቅረብ አለባቸው።
2. ከላይ በተራ ቁጥር አንድ የተገለጸው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 500 ሺህ በታች የሆነ ማንኛውም እቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አያስፈልግም እንዲሁም የሚሸጠው እቃ ተሽከርካሪ ሲሆን የተሽከርካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ፣ በተራ ቁጥር 1 ከተገለጹት እና ሌሎች መረጃዎች ጋር በማያያዝ በፖስታ የተጫራቹን ስም እና ፊርማ በግልጽ በመጻፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን 27/12/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡30 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
4. በሐራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ለመሳተፍ ለምድብ 2 አልባሳት ዘርፍ እቃዎች ብር 51,000 (ሃምሳ አንድ ሺህ ብር)፣ ለምድብ 4 ልዩልዩ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ለምድብ 5 ንጽህና መጠበቂያ ዘርፍ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለየብቻው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በቀጥታ አካውንት ቁጥር 1000296553216 በጋላፊ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም በማሰራት የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር አንድ የተገለጹትን መረጃዎች በመያዝ በቀን 27/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ መገኘት አለባቸው።
5. ከላይ በተራ ቁጥር 3 እና 4 በተገለጸው መሰረት በቂ የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ተጫራች መወዳደር ወይም መጫረት አይችልም።
6. በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሳጥኑ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ፣ ማሻሻል ወይም ራሱን ከውድድር ውጭ ማድረግ አይቻልም።
7. ለግልጽ ጨረታ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9፡00-12፡00 የእቃዎቹን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 27/12/2018 ጠዋት 3፡00 ድረስ በውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 መግዛት ይችላሉ።
9. ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ለናሙና ዕይታ የሚቀርቡበት ጊዜ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00-6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ9፡00-12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት የእቃዎቹን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ሳያዩ በሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት የለውም።
10. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ የጊዜ ሰሌዳ (ስኬጁል) መሠረት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ
|
የቅ/ጽ/ቤቱ ስም
|
የጨረታው አይነት
|
የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
|
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንና ሰዓት
|
|
1
|
ጋላፊ ጉምሩከ ግልፅ ቅ/ጽ/ ቤት
|
ግልጽ ጨረታ
|
እስከ 27/12/2018 ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ
|
በ27/12/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ተዘግቶ በእለቱ 3፡40 ሰዓት ይከፈታል
|
|
2
|
ጋላፊ ጉምሩከ ግልፅ ቅ/ጽ/ ቤት
|
ሐራጅ ጨረታ
|
እስከ በ27/12/2018ዓ.ም ከጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ
|
በ27/12/2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል
|
11. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- በጋላፊ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በተራ ቁጥር አንድ የተጠቀሱ ማስረጃዎች ኦርጂናል ይዘው መቅረብ አለባቸው።
12. በተጫራቾች የተሰጠ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚገለፅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
13. በጨረታ ለሚሽጥ እቃ የጨረታ ውጤት እንደተገለጸ ከአሸናፊው ጋር የሽያጭ ውል እንደተደረገ ይቆጠራል።
14. ምድብ ለወጣላቸው ሐራጅ እቃዎች ጨረታው የሚካሄደው በምድብ ሲሆን ተጫራቾች አሸናፊ የሚያደርጋቸው ለምድቡ ባቀረቡት የእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ ድምር ከፍተኛው ዋጋ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በምድቡ ለቀረቡት ለእያንዳንዱ እቃዎች ዋጋ መስጠት አለባቸው።
15. ተጫራቾች ከአሸነፉበት የእቃ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) የሚጨመር ይሆናል።
16. ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተመለከተለአሸናፊው ተጫራች ካሸነፉት የእቃ ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
17. አሸናፊው ተጫራች እቃዎቹን ባሉበት ቦታ እና ሁኔታ የመረከብ ግዴታ አለበት፡፡ በተጨማሪም ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይችላል።
18. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ05 (በአምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ያለበት ሲሆን ይህን ባይፈጽም ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመስሪያቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀርብ ሲሆን ነገር ግን አሸናፊው የአሸነፈበትን የእቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ እቃውን ያላነሳ እንደሆነ ለሚቆይበት ተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ የሚከፍል ይሆናል፡፡ ሆኖም እቃውን በሁለት ወር ውስጥ ካላወጣ ለንብረቱ የተከፈለው ዋጋ ለመስሪያቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው እንደተተወ ተቆጥሮ በሽያጭ ይወገዳል።
19. በጨረታ የሚሸጠው እቃ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከመወረሱ በፊት የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
20. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች የሚገኙበት ቦታ ጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መሆኑ ይታወቅ።
21. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ውርስ መጋዘን አስተደደር የስራ ሂደት ስልክ ቁጥር 033-559-0114 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
