በሽገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የገላን ከ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በሽገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የገላን ከ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ አላቂ የፅህፈት መሳሪየዎች፡የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤልክትሮኒከስ ዕቃዎች ፣በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. ተጫራቶች በጨረታ ለመከፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራች ከ100,000ብር ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ተመዝጋብ የሆኑና ለዚሁ መስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
3. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቶች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቶች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 150 (መቶ ሃምሳ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ለምን ለምን ዓይነት ዕቃ እንደ ሆነ በሰነዳቸሁ ላይ በትክከል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ፍ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard/ ውጪ ማቅረብ አይቻልም፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ነገር መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን መሰረዝ አይችልም፡፡
8. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡
9. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡ በ15ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ 4፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
10. ማንኛውም ተጨራች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 19% የጨረታ ማስከበርያ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
11. ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. የጨረታው ዋጋ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ መጥቀስ ይኖርበታል፡፡
13. ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋርይዋዋላል፡፡
14. የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሞልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡
አድራሻ፦ በገላን ከተማ ማዘጋጃ ቤት ፊትለፊት በሚገኝ የፍርድ ቤቱ ፎቅ ላይ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር: 0118871269 /0922817019
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የገሳን ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
