በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ማርች 8 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የአንደኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የአንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ማርች 8 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የአንደኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት-1 የደንብ ልብስ ግዢና ስፌት ሎት-2 የቢሮ እቃዎች ሎት-3 የተለያዩ ህትመቶች ሎት-4 የህክምናና የላይብረሪ እቃዎች፣ ሎት-5 የት/ርት እቃዎች ፣ ሎት-6 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት-7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መጽሔቶች ሎት-8 ፕላን ማሽነሪ ጥገና፣ ሎት-9 ህንጻ ቁሳቁስ ጥገና፣ ሎት-10) የጭነት አገልግሎት ፣ ሎት-11 ፕላን ማሽነሪ እቃዎች ግዢ፣ ሎት-12 ህንጻ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎች ግዢ እና ሎት-13 ለልዩ ልዩ ክፍያዎች በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውንና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ
| የሎት ቁጥርና ዝርዝር | በኢትዮጵያ ብር |
| 1. ሎት-1 የደንብ ልብስ ግዢና ስፌት | ብር 18,000 |
| 2. ሎት-2 የቢሮ እቃዎች | ብር 12,000 |
| 3. ሎት-3 የተለያዩ ህትመቶች | ብር 2,500 |
| 4. ሎት-4 የህክምናና የላይብረሪ እቃዎች | ብር 3,000 |
| 5. ሎት-5 የት/ርት እቃዎች | ብር 19,000 |
| 6. ሎት-6 የጽዳት እቃዎች | ብር 19,000 |
| 7. ሎት-7 ልዩ ልዩ መሳሪያዎችና መጽሐፍቶች | ብር 7,000 |
| 8. ሎት-8 ፕላን ማሽነሪ ጥገና | ብር 3,500 |
| 9. ሎት-9 ህንጻ ቁሳቁስ ጥገና | ብር 8,960 |
| 10. ሎት-10 የጭነት አገልግሎት | ብር 5,542.40 |
| 11. ሎት-11 ፕላን ማሽነሪ እቃዎች | ብር 20,000 |
| 12. ሎት-12 ህንጻ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎች | ብር 18,000 |
| 13. ሎት-13 ልዩ ልዩ ክፍያዎች | ብር 2,048.92 |
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 1 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን 9:00 ሰዓት ታሽጎ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፣
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበባቸው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ማርች 8 የመጀ/ደ/ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች ጨረታውን ሲሞሉ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
አድራሻ፡- ጃፓን ጴንባሲ ገባ ብሎ ማርች 8 የመጀ/ደ/ት/ቤት
በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ማርች 8 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for March 8 School in Bole sub-city covering 13 lots: uniforms, office supplies, printing, medical/library items, cleaning supplies, equipment, machinery repair, building materials, transport, and more. Bidders need valid licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
