በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር በጉጂ ዞን የኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር በጉጂ ዞን የኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ አላቂ የፅሕፈት ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ውሰጥ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የቴከኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ፣ ኤሌከትሮኒከስ ነከ እቃዎችን፤ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች እና የመሳሰሉትን ለ2019 ዓ.ም የበጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በየንግድ መስኩ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፍቃዳቸውን፣ አመታዊ የስራ ግብር የተከፈለበትን፣ በመንግስት እቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት እንዲሁም የተጨማሪ ስሴት ታክስ (ቫት)ና ቲን የተመዘገቡበትን የሚገልፅ መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ. 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ) ብር በመከፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር ለጨረታው ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 2% ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት በኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /CPO/ወይም ጥሬ ገንዘብ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ የጨረታ ዓይነቱን በግልጽ በመጻፍ ኮፒ እና ኦሪጂናሉን በመለየት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5/1/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.6 በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በ 5/1/2019 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.4 ይከፈታል::
- አሸናፊው እንደታወቀ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
- አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ በማጓጓዝ ኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግምጃ ቤት ማስገባት አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
* ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ.ቁ 046-471-0190/191 ይደውሱ፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር በጉጂ ዞን የሱራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement of various goods for the 2019 budget year: office supplies, cleaning materials, furniture, vehicle tires, staff uniforms, technical/vocational college teaching aids, electronics, and construction items. Bidders must hold a valid renewed trade license, tax clearance, and VAT/TIN registration.
